አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት ጁንታን የሚቃወምና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
በዚህ ንግግራቸውም ይሕ የምንገኝበት ታሪካዊ ምዕራፍ አጓጊውን የለውጥ ጅማሯችን የሚያሰጋቸው የውስጥ ባንዳዎች እና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ግንባር ፈጥረው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙበት ነው ብለዋል።
በዚህም ሉዓላዊነታችንን ለመዳፈር ፣ ሀገራዊ አንድነታችንን እና የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ ለማደናቀፍ የሞት ሽረት እያደረጉ ነውም ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ።
“ይሁን እንጂ ወትሮም ቢሆን ለየትኛውም ምድራዊ ሀይል በፍቅር እንጂ በሃይል የማይንበረከከው ህዝባችንን ይዘን የሚያጋጥሙን ፈተናዎችን ሁሉ በድል እንሻገራለን” ሲሉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ መሰረት የተከለችበትን ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ፣ የታላቁን የህዳሴ ግድባችንን ሁለተኛውን ሙሌት በድል በማጠናቀቅ በዓለም መድረጀክ ጭምር በአሸናፊነት ደምቃ የተወጣችበትን ድሎች መጥቀስ ይቻላልም ነው ያሉት።
በዚህም ለዓለም ትምህርት የሰጠንበት እና ሉአላዊነታችንን ለመድፈር ለሚመኙትን ሁሉ አይበገሬነታችንን ያሳየንበትም ድል ነው ሲሉም ገልጸዋል ።
የዚህ አንጸባራቂ ድል ባለቤት የሆነውን ጨዋውንና አይበገሬውን ህዝባችንን ዝቅ ብለን እናመሰግናለን ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

