Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ህወሓት ህፃናትን ለጦርነት መማገዱን ሊያወግዝ ይገባል – ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ህወሓት ህፃናትን ለጦርነት መማገዱን ሊያወግዝ እንደሚገባ የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ጉዳዩን አስመልክቶ ባሰፈረው መልዕክት÷ ህወሓት የሽብር ቡድን ዕድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህጻናትን ወደ ጦርነት እየማገደ ስለመሆኑ በማስረጃ የተደገፉ በርካታ መረጃዎች እየወጡ መሆኑን አንስቷል፡፡
ይሁን እንጂ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በጉዳዩ ላይ ዝምታን መምረጡን ነው ያመላከተው፡፡
ስለሆነም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ቅሪቶች ንጹሃን ልጆቻችንን በማስገደድ ለጦርነት የሚማግዱበትን ሁኔታ ሊያወግዝ ይገባል ነው ያለው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version