Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አብን የአማራ ክልል መንግስትን የክተት ጥሪ በሙሉ ልብ እንደሚቀበለው አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ክልል መንግስትን የክተት ጥሪ በሙሉ ልብ እንደሚቀበለው አስታውቋል፡፡

ፓርቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ለአማራና ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፣

ለተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች፡-

ድርጅታችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገር ሉዓላዊነትና  አንድነትን ለማስጠበቅ፣ ህግና ስርዓትን ለማስፈንና ሀገርን ለማዳን የጀመረውን ጥረትና  የክልል መንግሥታት እያደረጉት ያለውን ቁርጠኝነት የተሞላበት የተባበረ እንቅስቃሴ ንቅናቄያችን በአክብሮት ይመለከተዋል።

የአማራ ክልል መንግስት ከፍተኛ የሆነ የህልውና ስጋት የተጋረጠበትን ሀገረ መንግሥትና በጠላትነት የተፈረጀውን ሕዝባችን ለመታደግ የአወጀውን የክተት ጥሪ በሙሉ ልብ የምንቀበለውና  ለተግባራዊነቱም የበኩላችን ከፍተኛ ጥረት የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን፣

የክልሉ መንግሥትም አልፎ አልፎ የሚታዩ አስተዳደራዊ ችግሮችን በመፍታት የመሪነት ሚናውን በተገቢው መንገድ እንዲወጣ እንጠይቃለን።

መላው የድርጅታችን አመራሮች አባላት ደጋፊዎቻችንና ሕዝባችን ይህን ጥሪ በመቀበል በየደረጃው ካለው መንግሥታዊ መዋቅር ጋር በመቀናጀት  የክተት ዘመቻውን እንድትቀላቀሉ እናሳስባለን ።

እሁድ ሐምሌ 18 ቀን  2013 ዓ.ም

 

Exit mobile version