Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች በየአየር ጸባይ ምክንያት አቅራቢያ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ በተፈጠረው መጥፎ የአየር ጸባይ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች አቅራቢያ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልከቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት÷ በተፈጠረው መጥፎ የአየር ጸባይ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ በረራዎች አቅራቢያ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ እየተደረገ ነው፡፡

የተፈጠረው አየር ጸባይ ችግር ሲስተካከል ለደንበኞቹ እንደሚያሳውቅም ነው አየር መንገዱ የገለጸው፡፡

ከአየር መንገዱ አቅም በላይ ለተፈጠረው ችግርም ደንበኞችን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version