አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ግዳጁን በመፈፀም ላይ የሚገኘው የ2211ኛ ሻለቃ ሰራዊት አባላት የመንግስትን ጥሪ አልቀበልም በማለት በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ሃይሎች ላይ እርምጃ ወሰደ፡፡
የ2211ኛ ሻለቃ ዋና አዛዥ ሻለቃ ዮሃንስ እውነቱ እንደተናገሩት ÷ከሀገር ሰላም በተቃራኒ በመሆን እና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ወደ ጎን በመተው ህዝቡ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዳይገባ የጥፋትን ተልዕኮ እየፈፀሙ ባሉ ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ 25 የሽፍታ አባላትን ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርኳቸዋል ፡፡
ጠላት ታጥቆ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ዘጠኝ ክላሽ መሳሪያ፣ሶስት ኋላ ቀር መሳሪያ እንዲሁም በርካታ ቀስቶችን መማረካቸውንም አስረድተዋል ፡፡
በተጨማሪም 185 የክላሽ ጥይት ፣16 የብሬን ጥይትና አንድ የእጅ ቦምብ ይዘው በህብረተሰቡ ላይ ጥቃት ለማድረስ ቢያስቡም ሰራዊቱ ቀድሞ በመንቃት ድል ማድረጉን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

