አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሽብር አላማ በ2 ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሣሪያ መያዙን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት እና ከህብረተሰቡ ጋር ባደረገው ክትትል ለተለያዩ የሽብር አላማዎች ማሳኪያ በ2 ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረውን 35 ክላሽንኮቭ መሣሪያዎች ከካርታዎች ጋር እንዲሁም ከ 3 ተጠርጣሪዎች ጋር ነው በቁጥጥር ስር ለማዋል የተቻለው፡፡
ሲጓጓዝ የነበረውን የጦር መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በደቡብ ክልል ቡታጅራ ከተማ ሲደርስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አንዱ ተጠርጣሪ ለጊዜው በመሠወሩ ክትትል እየተደረገ እንደሆነም የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

