አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ዘመቻው የሀገር ህልውና ጠብቆ ለማስቀጠል የሚደረግ በመሆኑ ለስኬታማነቱም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጽያን ለመከፋፈልና ለውጭ ጠላቶች አሳልፎ ለመስጠት ስልጣን ከለቀቀበት ጊዜ ጀምሮ በሽብር ድርጊት በመሰማራት የጥፋት ተልኮ ሲፈፅም ቆይቷል ብለዋል፡፡
አያይዘውም ጁንታው የአማራን ህዝብ በተለየ ሁኔታ እንደ ጠላት በመቁጠር ለግማሽ ምዕተ ዓመት ግፍ ሲፈፀምበት ነበር ብለዋል፡፡
ይህ እንዳይደገም የአማራ ህዝብ የክተት አዋጁን በመቀበል ኢትዮጽያን ለማዳን ፈጣን ምላሽ መስጠት ይገባዋል ነው ያሉት፡፡
የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው ግንባር ለተሰለፈው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚኒሻ እና ፋኖ ስንቅ በማዘጋጀት ደጀን ከመሆን ባለፈ ግንባር ሄደን የሚጠበቅብንን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ነዋሪዎቹ አሜሪካና የአውሮፖ ህብረት እንዲሁም አንዳንድ ዓለማቀፋዊ ተቋማት ኢትዮጽያን ለማፍረስ የሚያቅዱትን ሴራም አውግዘዋል፡፡
በኢሳያስ ገላው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

