Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቦንጋ ከተማ የህወሓት ጁንታ ቡድንን ሀገር የማፍረስ ሴራ የሚያወግዝ ሠልፍ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የህወሓት ጁንታ ቡድንን ሀገር የማፍረስ ሴራ የሚያወግዝ እና የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌትን የሚደግፍ ሠላማዊ ሠልፍ እየተደረገ ነው፡፡
በሠልፉ ላይ ህወሓት የመላ ኢትዮጵያዊያን የእድገት፣የአብሮነት እና የሠላም ፀር ነው፤ በዚህም ሁሉም ኢትየጵያዊያን በጋራ ሊፋለመው እደሚገባ ሰልፈኞች ጠይቀዋል፡፡
በሰልፉ የክልል ልዩ ሃይሎችን የሚያመሠግኑ፣ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚኮንኑ እና የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሀ ሙሌትን የደሥታ ሥሜት የሚገልጹ መልዕክቶች ተንጸባርቀዋል፡፡
ሰልፈኞቹ ሃገር የማዳን ተግባራቸውን በተግባር እንደሚወጡ እና ድጋፋቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
በሠላማዊ ሠልፉ ላይ የወረዳወች እና የዞን ነዋሪዎች እና አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በተመስገን ይመር
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version