አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ወሎ ዞን የዘመቻ ህልውና የክተት ጥሪ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በንቅናቄ መድረኩ ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሰሀ ወልደሰንበትን ጨምሮ የፌዴራል የክልል እና የዞኑ የሥራ ኀላፊዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው በዚህ ወቅት እንደገለጹት፥ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ለማዳን ወሎ ላይ የሚደረገው ትግል ወሳኝ ነው፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው፥ አሁን የምንገኝበት ወቅት ዓለምአቀፍ ድል የተቀዳጀንበት በሌላ በኩል ደግሞ የውስጥ እና የውጭ ጠላት ሀገራችንን ለመጠበቅ የተዘጋጀንበት ነው ብለዋል፡፡
የሥራ ኀላፊዎች ራሳቸውን የማዘጋጀት፣ ኅብረተሰቡን የማደራጀት እና የማንቃት ሥራ መሥራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሰሀ ወልደሰንበት በአሁኑ ወቅት ማኅበረሰቡ አሁን የቀረበለትን የክተት ጥሪ ተቀብሎ እንዲዘምትም ነው ጥሪያቸውን ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎችም አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለማጥፋት የክተት ጥሪውን ተቀብለው ለመዝመት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

