አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሊመዘበር የነበረ ከ80 ሚሊየን ብር በላይ በቅድመ መከላከል ስራ ማዳን መቻሉን የደቡብ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽነር ኑሪየ ሱሌ በህገ -ወጥ መንገድ ሊመዘበር የነበረውን 30ሺህ ካሬ የከተማ መሬት ማዳን እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡
በበጀት አመቱ ከ232ሺህ በላይ በክልሉ ያሉ የመንግስት ተሿሚዎችና ሰራተኞች ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በ2014 በጀት ዓመትም የተጀመሩ ተግባራትን አጠናክሮ ለመሄድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመግባባት ወደ ስራ እንደተገባ ጠቁመዋል ።
በተመሳሳይ የኮሚሽኑ አጠቃላይ ሰራተኞች በወላይታ ዞን የችግኝ ተከላ ፣ለአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት እንዲሁም ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል ።
በማቲዎስ ፈለቀ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

