Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በትግራይ ያለው የምግብ ክምችት አርብ ያልቃል – የዓለም ምግብ ፕሮግራም

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በትግራይ ያለው የምግብ ክምችት በሚቀጥለው አርብ እንደሚጠናቀቅ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለጸ፡፡

የፕሮግራሙ ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊይ፥ በትግራይ የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እርዳታውን ለማቅረብ በቀን 100 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

አክለውም በአሁኑ ወቅት ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን የጫኑ 170 ተሽከርካሪዎች አፋር ላይ መቆማቸውን እና መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ሰዎች ለምግብ እጥረት እየተጋለጡ ነው ያሉት ዴቪድ ቢዝሊይ፥ አሁን ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ሊፈቀድላቸው ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version