አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ በዓይነትና በገንዘብ በድምሩ ከ37ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊት አድርጓል፡፡
በክልሉ ተወክለው ቦታው ላይ ተገኝተው ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፉን ያስረከቡት የደቡብ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኸኝ ሽፋ፥ ክልሉ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ ከ250 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት በተለያየ መልኩ የሚገለፅ የመከላከያ ድጋፍ ለማድረግ እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም ደረቅ ምግቦችና ለተለያዩ ግልጋሎቶች የሚውሉ የፋብሪካ ውጤቶችን ጨምሮ ከ400 በላይ በጎችና ፍየሎችን እንዲሁም ከ155በላይ ሰንጋዎችን ለመከላከያ ሰራዊቱ ማበርከቱን አንስተዋል፡፡
ቦታው ላይ ተገኝተው ድጋፋን የተረከቡት በኢፌዴሪ መከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ የፋይናንስ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴል ጀነራል አስረስ አያሌው ለመከላከያ ሰራዊቱ በተለያየ መልኩ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡
በዛሬው እለትም የደቡብ ክልል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ በአይነትና በገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አንስተዋል፡፡
ይህ ደግሞ ለመከላከያ ሰራዊቱ ትልቅ ብርታትን የሚሰጥ በመሆኑ አመስግነው፥ በተጀመረው አግባብም በተለያየ መልኩ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በትዝታ ደሳለኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

