አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 21፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መንግሥትን የክተት ጥሪ በመቀበል በባሕር ዳር ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።
በሰልፉም በአማራ ላይ የሚወራረድ አንድም ሒሳብ የለም፤ የእድገት ጉዟችን በአሸባሪው ቡድን አይደናቀፍም፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚመኙ ሁሉ መጨረሻቸው ውድቀት ነው፤ የጁንታው ሀገር የማፍረስ ፍላጎት በኢትዮጵያ አሸናፊነት ይከሽፋል፤ ኢትዮጵያ በጀግኖች አፍራ አታውቅም፤ የምንዋጋው ለህልውናችንና ሀገር ለማዳን ነው፤ የውጭ ጣልቃ ገብነትን እንቃወማለን የሚሉ መልዕክቶች መስተጋባታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

