አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪውን የህዋሃት ቡድን የሚቃወምና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ እና ገሱባ ከተማ ተካሂዷል ፡፡
«አንድ ሆነን ታሪካዊ የኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ጠላቶቿን የምንመከትበት ወሳኝ ጊዜ ላይ እንገኛለን፤ የህውሐት ጅንታ ቡድን ሴራ ለማክሽፍ ምንም ዓይነት ልዩነት ልኖር አይገባም፤በሀገር ህልውና ላይ የመጣውን ጠላትን በማሸነፍ ለዓለም ማህበረሰብ አንድነታችን ማሳየት ያስፈልጋል… » የመሳሰሉትን መፈክሮችን በመያዝ ሰልፈኞች የድጋፍ ድምፃቸዉን አሰምተዋል፡፡
በድጋፍ ሰልፍ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኦፋ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አካሉ ባፋ፥ አሸባሪውን የህዋሃት ትንኮሳ በማክሸፍ የህግ በላይነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዉ፥ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ከምን ጊዜዉ በላይ ተጠናክሮ መታየት አለበት ብለዋል፡፡
የገሱባ ከተማ ከንቲባ ቀሲስ ጥበቡ በቀለ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ በወያኔ ሴራ እንደማትፈርስ ማረጋገጥ ስለሚያስፈልግ ዛሬ ላይ በከተማዉ የታየዉ የድጋፍ ሰልፍ በሌሎች ሃገራዊ አንድነቶች ላይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል፡፡
ሁሉም የከተማዉ ነዋሪዎችም በሚችሉት ሁሉ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ለመከላከያ ሰራዊትም በገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን፥ ወጣቶች የሃገር ጥሪን ተቀብለው እየተዘጋጁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በማቴዎስ ፈለቀ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

