አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘይት ፋብሪካዎችን የግብዓት እጥረት ለመቅረፍ 89 ሺህ 248 ቶን በላይ የአኩሪ አተርና የፓልም ድፍድፍ ዘይት መቅረቡን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለውን የምግብ ዘይት አቅርቦትና ፍላጎት አለመመጣጠን ችግር ለመቅረፍ በሀገር ውስጥ ያሉ የዘይት ፋብሪካዎችን ቁጥርና የማምረት እቅም ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡
ፋብሪካዎቹ ያለባቸውን የጥሬ እቃ እጥረት ለማቃለልና የማምረት ስራቸውን ሳያቋርጡ የምግብ ዘይት አቅርቦቱ ላይ ያለውን ክፍተት በመሙላት በኩል ያላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል በ2013 በጀት ዓመት 89 ሺህ 248 ነጥብ 8 ቶን የአኩሪ አተርና የፓልም ድፍድፍ ዘይት ከውጪ ተገዝቶ ቀርቧል፡፡
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ በምግብ፣ መጠጥ፣ ፋርማሲዩቲካል እንዲሁም ስጋና ወተት ዘርፍ የተሰማሩ ፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ወደ 65 በመቶ ለማሳደግ የታቀደ ቢሆንም በተደረገው ክትትልና ድጋፍ ወደ 48 በመቶ ማሳደግ መቻሉን የአግሮ ፕሮሰሲንግና ፋርማሲዩቲካል ዳይሬክተር አቶ አለሙ ሎቤ ገልፀዋል፡፡
በዘርፉ ለ44 ሺህ 661 ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ÷ ለ32 ሺህ 953 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

