አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ዞን አራት እዋ በተባለ ወረዳ በተወሰደ የማያዳግም እርምጃ የሽብርተኛው ሕወሓት ቡድን አከርካሪ ተመትቷል።
በውጊያው ቡድኑ ያሰለፋቸው በርካታ ታጣቂዎች ተደምስሰዋል፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማርከዋል፡፡
ጁንታውን ከአካባቢው ጠራርጎ ለማስወጣት የአፋር ልዩ ኃይልና መከላከያ ሠራዊት በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ የተማረኩ የጁንታዉ አመራሮች በሰጡት ቃል እምቢተኛው የሽብር ቡድን ሕወሓት በአፋር ክልል በድምሩ ሦስት ክፍለ ጦሮችን አሰማርቶ እንደነበር አስረድተዋል።
አንደኛው ክፍለ ጦር በተወሰደበት ከባድ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ መደምሰሱን አረጋግጠዋል፡፡
የአሸባሪው ቡድን የተቀሩት ሁለቱ ክፍለ ጦሮች ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የቀለብ፣ የጥይትና መሰል የሎጀስቲክስ አቅርቦት ችግር ውስጥ እንዳሉ ምርኮኛ አመራሮች ማስረዳታቸውን ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

