Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የወልዲያ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ጸጥታ በንቃት እየጠበቁ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪውን የትህነግ ሴራ ለማክሸፍ የወልድያ ወጣቶች ከከተማው ማኅበረሰብ ጋር የከተማዋን ጸጥታ በንቃት እየጠበቁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዚህም እስካሁን ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን እና የነዋሪው የዕለት ተዕለት ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ወጣቶቹ የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅና ሰርጎ ገቦችን በመከታተል ለሕግ እያቀረቡ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መሐመድ ያሲን የከተማው ወጣቶችና ማኅበረሰቡ አሸባሪው የትህነግ ቡድን የከፈተውን ጦርነት ለመመከት እስካሁን ያደረጉት ተግባር ታሪክ የማይረሳው ነው ብለዋል፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጋሻው አስማሜ ኅብረተሰቡ የአሸባሪው ትህነግ ቡድን በሚነዛው የሐሰት መረጃ ሳይደናገር የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ መልእክት አስተላልፈዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version