አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዞብል አሉሙኒየምና ሞል እህት ኩባንያ ለህልውና ዘመቻው የሚውል ግምቱ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያየ ቁሳቁስ ለጎንደር ከተማ አስተዳደር አስረከበ።
የኩባንያው ባለቤት አቶ እንዳልካቸው መኮንን በአሸባሪው ህወሓት ቡድን የተቃጣውን ጦርነት ለመመከት ግንባር ለሚዋጉ ሀይሎች ከአሁን ቀደም የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
በሁለተኛው ዙርም ተቋማቸው ለመከላከያ ሀይሉ አገልግሎት የሚውሉ 15 ሺህ ኩንታል ቴምር፣ 1 ሺህ ብርድ ልብስና 1ሺህ የዝናብ ልብስ ግምቱ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
ድጋፉን ለከተማ አስተዳዳሩ ምክትል ከንቲባና ለሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተሾመ አግማስ አስረክበዋል።
የከተማው ምክትል ከንቲባና የህልውና ዘመቻው ሀብት ሰብሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ተሾመ አግማስ ባለሀብቱ በሁለት ዙር ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊቱ አድርገዋል ብለዋል።
ባለሀብቱ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት አቶ ተሾመ አግማስ ሌሎች የከተማዋ ባለሀብቶችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የከተማው ባለሃብቶች ከ21 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ሰብሳቢው ገልፀዋል።
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

