አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ39 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ከብክነት ማዳን መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ከገቢ እና ወጪ ንግድ ጋር በተያያዘ ለደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ለቢዝነስ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር የታመነበት የኢትዮጵያ የአንድ መስኮት አገልግሎት ስርዓት ስራ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡
በ2013 በጀት ዓመት የዝግጅት ምእራፍ በአንድ መስኮት አገልግሎት ከተከናወኑት ተግባራት መካከል የመጀመሪያ ዙር የሶፍትዌር ልማት ተጠናቆ ወደ ትግበራ ተገብቷል፡፡
በአንድ መስኮት አገልግሎት የተስተናገደ የገቢ ንግድ 64 ሺህ 604 ሲሆን፥ የወጪ ንግድ ደግሞ 5 ሺህ 97 ሆኗል፡፡
በዚህ መሰረት 39 ሚሊየን 475 ሺህ 980 የአሜሪካ ዶላር ከብክነት ማዳን መቻሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በዚህም መሰረት የሙስና ተጋላጭነት የቀነሰ ሲሆን፥ ስርአቱ ለተገልጋዩ ከፍተኛ በሆነ መልኩ ጊዜና ወጪን ቆጥቧል ተብሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

