አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ክብርና ሉኡላዊነትን ለማስከበር ዜጎች እያሳዮት ያለው ተነሳሽነት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል አሉ ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የህግና የደህንነት ምሁራን እንዳሉት፥ የሽብር ቡድኑ የከፈተው ጦርነት በሀገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ የመጣ አደጋ እንደመሆኑ ኢትዮጵያን ለማዳን ለመከላከያ ሰራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ መጠናከር አለበት ብለዋል።
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የህግ መምህሩ አቶ ዘመድኩን መካሻ፥ የሽብር ቡድኑ ሀገር በመበታተን የኢትዮጵያን ሉኡላዊነት የደፈረ፤ ህዝቦቿን ለእልቂት ለመዳረግ የሚታትረው ሀይል ግልጽ የሉኡላዊነት ጦርነት በገዛ ሀገሩ ላይ መክፈቱን ተናግረዋል።
የሀገር ባንዳ የሆነው የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ከውጭ ሀገራት ለሚቃጣ የሉአላዊነት መደፈር ጭምር የዳረገ ስለመሆኑም ገልጸዋል።
የሰላምና ደህንነት ተንታኝ የሆኑትን ዶክተር መሳይ ሀጎስ፥ የውትድርና ፍቅር መነሻዎች ለሀገር መዋደቅና ሀገር ከፍ ብላ እሱ ትቢያ ሆኖ እስከመቅረት ድረስ የሚገለጽ በመሆኑ ለመከላከያው ድጋፉ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
የሽብር ቡድኑ በስልጣን በነበረባቸው ዓመታት የኢትዮጵያን የአርበኝነት ገድሎች የሚያንቋሽሽ ፤ ቀደምት አባቶች ለሀገር አንድነት የከፈሉትን መስዋእትንት አድበስብሶ በማለፍ ወጣቱ ምንም የሀገር ፍቅርና ወኔ እንዳይኖረው መስራቱንም ጠቅሰዋል።
ሆኖም ከሰሞኑ በሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ ያለ ወጣት ለሀገሩ ክብር ለመዋደቅ ሰንደቁን ይዞ መነሳቱ የሚደንቅ ነው ብለዋል።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የህግ እንዲሁም የሰላምና ደህንነት ምሁራን፥ ለሀገር ክብርና ሉኡላዊነት በሚከፈል ዋጋ ቀደምት አባቶች ደምና አጥንታቸውን የከፈሉባትን ሀገር በአንድነት አለት ላይ ማስቀመጥ ይጠበቃል ብለዋል።
ሀገሩን ለማዳን እየዘመተ ያለው ወጣትም በሀገር ፍቅር ውስጥ ሆኖ የአባቶቹን ገድል መድገም ይገባዋል ነው ያሉት።
በሀይለየሱስ መኮንን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

