Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት የ2014 ዓ.ም ረቂቅ በጀት 2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ እንዲሆን ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት የ2014 ዓ.ም የክልሉ መንግስት ረቂቅ በጀት 2 ቢሊየን 983 ሚሊየን 703 ሺህ 873 ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ለሁለት ቀናት ሲያካሄድ የነበረው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል።

ምክር ቤቱ የ2013 የክልሉ የዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም የ2014 ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በመወያየት ማጽደቁን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የ2014 የክልሉ መንግስት ረቂቅ በጀት 2 ቢሊየን 983 ሚሊየን 703 ሺህ 873 ብር እንዲሆን ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን÷ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ 19 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡

የዚህ በጀት ምንጭ በዋናነት ከክልሉ ግብር ከፋዮች የሚሰበሰብ ገቢን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን÷ የክልሉ ገቢ ዕቅድ በ2013 ከነበረዉ ሲነጻጸር በ2014 የ 21 በመቶ ዕድገት እንደሚኖረው ታሳቢ ተደርጓል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version