Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዳንጉር ወረዳ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን የዳንጉር ወረዳ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።
የህዝባችን አብሮነት እና አንድነት ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የጁንታውን ቡድን በጋራ እንታገላለን በሚል መሪ ቃል ነዋሪዎች ለሰራዊቱ የድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ጁንታውን የሚያወግዙና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደገፉ እንዲሁም ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ መልዕክቶች ተንጸባርቀዋል።
ኢትዮጵያ ከውጭና ከውስጥ የተቃጣባትን ጦርነት ለመመከት ሀገር የመከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ በተዋረድ ያለው የጸጥታ አካላትና መላው ህብረተሰብ በመረባረብ ጁንታውን ማስወገድ እንደሚገባ የዳንጉር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ክንፉ ተናግረዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገቢዎች ዋና ዳይሬክተር አቶ መለሰ ኪዊ በበኩላቸው ሀገርን ለማፍረስ ጠላት የያዘውን አጀንዳ በአንድነት ልንመክት ይገባል ማለታቸውን ከመተከል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version