Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በ10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘቷ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ኮማንደር ደራርቱ ውጤቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ለመላው የሀገሪቱ ህዝብ በራሴና በኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚና ማኔጅመንት ኮሚቴ፣ አሰልጣኞችና ሰራተኞች ስም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ለስምንት የዝግጅት ወራት ከፌደሬሽኑ ጎን ለነበሩ አካላት ምስጋና ማቅረባቸውንም ከኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version