Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ 583 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና ድህረ ምረቃ መርሐግብር ያሰለጠናቸውን 583 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 135ቱ ሴቶች ሲሆኑ 448ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና ሃገሪቱ በውስጣዊ ችግር እና በውጭ ጫና ተወጥራ ባለችበት በአሁኑ ወቅት ተመራቂዎቹ የመፍትሄው አካል አንዲሆኑና ሙስናን በመጠየፍ ህብረተሰቡን በትጋት እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ከሚያሰለጥናቸው በተጨማሪ በሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን በዝግጅት ላይ መሆኑን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version