አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጎጃም የተለያዩ አካባቢዎች የክተት ጥሪውን በመቀበል ወደ ዘመቻ እያቀኑ ነው፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን አማራን ለማጥፋትና ኢትዮጵያን ለመበታተን የከፈተውን ጦርነት ለመመከትና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ከምዕራብ ጎጃም ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የፋኖ አባላት ወደ ጦር ግንባር ዘምተዋል፡፡
ለፋኖ አባላቱ በፍኖተ ሰላም ከተማ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
“የአባቶቻችንን የአርበኝነትና የፋኖነትን ታሪክ በመድገም አሸባሪውን በመደምሰስ የሀገሪቱን ሰላም እናስጠብቃለን ” ያሉት አባላቱ የመንግሥትን የክተት ጥሪ ተቀብለው መዝመታቸውን ተናግረዋል፡፡
መቶ አለቃ አሰፋ አድማሱ ከምዕራብ ጎጃም ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች የመንግሥትን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ግንባር እየዘመተ ያለው ፋኖ አባላት አስተባባሪ ናቸው፡፡
አሸባሪው የትህነግ ቡድን አማራን በማጥፋት ሀገሪቱ እንድትበታተን ለመመስረት እየታተረ መሆኑን ጠቅሰው፥ የፋኖ አባላትም ይህንን ቀድሞ ይረዳ ስለነበር የአሸባውን ትህነግ ሴራ ለመበጣጠስ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
“ፋኖነት ለኢትዮጵያ እና ለነጻነት መስዋዕት መሆን ነው” ያሉት መቶ አለቃ አሰፋ፥ መንግሥት ባቀረበው የክተት ጥሪ መሠረት አባላቱ ለእናት ሀገራቸው መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡
የፋኖ አባላቱ የመንግሥትን ጦር የሚመራው አካል በሚያሰማራው ግንባር በመሰለፍ ትህነግን ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

