Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመተከል ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን የፓዊ ወረዳ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል።

ነዋሪዎቹ አጥፊው የጁንታ ቡድን በኢትዮጵያ እየሰነዘረ ያለውን ድርጊት በማውገዝ ለሰራዊቱ ያላቸውን ደጀንነት በድጋፍ ሰልፍ ገልጸዋል።

የህወሓት አሸባሪ ቡድን ለዘመናት በህዝብ መካከል የፈጠረውን የመለያየት ተግባር በማውገዝና አንድነትን በማጠናከር የኢትዮጵያ ህልውና ለማስጠበቅ እንደሚሰሩም የፓዊ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበር ላይ የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ ዘብ እንደሚቆሙም አክለው ገልጸዋል።

ቀጠናው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚገነባበት በመሆኑ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ከግብ እንዲደርሱ እንደሚሰሩ በድጋፍ ሰልፉ የተሳተፉ የፓዊ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተለያዩ አንድነትንና ጠላትን የሚያወግዙ መልዕክቶች መንጸባረቃቸውን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version