Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ካምፓስ 2 ሺህ 732 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 2ሺህ 732 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርስቲው ዛሬ ካስመረቃቸው 2ሺህ 732 ተማሪዎች ውስጥ 949 ሴቶች ሲሆኑ፥ በሁለት ኮሌጆች በ22 ቅድመ ምረቃ እና በአምስት ድህረ ምረቃ መርሃግብር ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አለሙ ሰሜ፥ ተመራቂ ተማሪዎች በግቢ ቆይታቸው ከቀሰሙት እውቀት ባሻገር በሀገር ፍቅር ስሜት ሀገራቸውን እንዲያገለግሉም አሳስበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር አፀደ ተፈራ፥ ተመራቂ ተማሪዎች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ለሀገራቸው ሁለንተናዊ እድገት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በ13ኛው ዙር የወሎ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች መረቃ መርሃግብር ላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪና የቀድሞው የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አባተ ጌታሁንን ጨምሮ የደሴ ከተማ ከንቲባ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version