አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የጎንደር ዩንቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎች እና የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጥብቅ ትስስር የሚፈጥሩበት የጎንደር ቤተሰብ ፕሮጀክት 2ኛ ዙር የቃልኪዳን ቤተሰቦች የትውውቅ መርሃግብር ተካሂዷል።
የቤተሰብ ትስስሩ ውጤታማ እንደነበር በመጀምሪያው ዙር አይተናል ያሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶክተር አስራት አጸደወይን፥ አላማውም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ወደዩኒቨርስቲያችን የመጡ ተማሪዎች የእንግድነት ስሜት እንዳየኖራቸው፣ የባህልና የቋንቋ ትስስርን ለማጠናከር ብሎም የእንግዳ ተቀባይነት ባህላችንን ለማሳደግ ነው ብለዋል።
ወላጆችም ጎንደር ላይ ልጆቻቸው ያለስጋት እንደሚማሩ አምነው የሚያስብላቸው ወላጅ በመኖሩ በነጻነት ልጆቻቸውን እንደሚልኩ ገልጸዋል።
የገበታ ለሃገር ፕሮጀክት አንዱ የሆነው የጎርጎራ ፕሮጀክት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተሰራው ማስተር ፕላንም ርክክብ ተደርጓል።
በሰላም አስመላሽ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

