Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሜሪካ በኢትዮጵያ እና አፍሪካ ላይ እየተከተለችው ያለው የተሳሳተ ፖሊሲ ነው – ሎውረንስ ፍሪማን

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አሜሪካ በኢትዮጵያ እና አፍሪካ ላይ እየተከተለችው የምትገኘው የተሳሳተ ፖሊሲ መሆኑን አሜሪካዊው የአፍሪካ ጉዳዮች ተንታኝ ሎውረንስ ፍሪማን ገለጹ፡፡

ተንታኙ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እየተከተለች ያለችው ልክ ያልሆነ ፖሊሲ ነው ያሉ ሲሆን፥ ይህንንም ማስተካከል ይጠበቅባታል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቀጠናው እራሷን ችላ የመልማት ፍላጎትና የ110 ሚሊየን ዜጎቿን ኑሮ ለመሻሻል የምትጥር ሃገር መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

‘‘አሁን ያለው የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ እየተከተለ ያለው ፖሊሲ በአስገራሚ ሁኔታ የተዛባ ነው’’ ሲሉም ነው ገለጹት፡፡

ኢትዮጵያ 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በሰላም ማጠናቀቋን እና በተፈጥሯዊ መንገድ ሁለተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ትልቅ ተግባራትን መፈጸሟን ገልጸው፥ ሆኖም ለስኬቱ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆባይደን እስካሁን የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት እንኳ አልተላለፈም ሲሉ ግርምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡

ሆኖም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ነፃ ፣ ፍትሃዊ እና ሰላማዊ ምርጫን መከናወኑን ተከትሎ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፥ “አሜሪካ ሰኔ 14 ላይ የመምረጥ መብታቸውን የተጠቀሙትን ታመሰግናለች” ማለታቸውን አስታውሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ውስጥ አንድም ግለሰብ አልሞተም ያሉት ተንታኙ፥ በንጽጽር አሜሪካ ባካሄደችው ምርጫ በርካቶች ለህልፈት መዳረጋቸውን አውስተዋል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕን ፈለግ በመከተል የባይደን አስተዳደር እና ዴሞክራቱ የሚቆጣጠረው ኮንግረስ፥ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሙሌት እንዳታከናውን ተስፋ ለማስቆረጥ መሞከራቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ያላት ወሳኝ ሚና ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የለውጥ እንቅስቃሴ እና የብልጽግና ፓርቲያቸው ስኬታማ ቢሆንም የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያይተው አያውቁም ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version