አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኦሞ ዞን ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል የወሰኑ ወጣቶች ሽኝት ተደርጓል፡፡
ሽኝት የተደረገላቸው ወጣቶች እንዳሉት “ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመሆን የሀገራችን ሉዓላዊነት ለማስከበር ተዘጋጅተናል”።
የደቡብ ኦሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ አረጋ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት “ወጣቶች እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትበተንም፤ በማለት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም በሀገር ላይ የተቃጣን ጥቃት ለመመከት ያሳዩት ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ብለዋል።
“ኢትዮጵያ ያሸናፊነት እንጂ የተሸናፊነት ታሪክ የላትም” ያሉት አቶ ብርሃኑ “ሀገራችንን ለማፈራረስ የሚርመሰመሱ ጠላቶቻችንን በማንበርከክ በታሪክ የወረስነውን ጀግንነት በተግባር እንደምናሳይ አንጠራጠርም” ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
አቶ ብርሀኑ ወጣቶቹ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት በመወጣት የእናት ሀገራቸውን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው ሰቅለው በድል እንደሚመለሱ እምነታቸውን በመግለጽ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማን ለወጣቶቹ ማበርከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

