Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 6ኛ አመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛና ማጠቃለያ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡
በጉባኤው የክልሉ መንግስት የ2014 በጀት ዓመት የስራ እቅድ የሚያቀርብ ሲሆን፥ የክልሉ መንግስት የ2014 በጀት በክልሉ ምክርቤት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የክልሉ ምክር ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፤ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2013 አፈጻጸምና የ2014 በጀት አመት እቅድም የሚቀርብ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም ልዩ ልዩ አዋጆች ይጸድቃሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ለዳኞች ሹመት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version