አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለመትከል ከታቀደው 6 ቢሊየን ችግኝ ውስጥ 5 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኝ መተከሉን ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ከተተከለው 5 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኝ ውስጥ የፍራፍሬ ችግኞች በብዛት መተከላቸውን በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ አጠቃቀም ዳይሬክተር ተፈራ ታደሰ ገልፀዋ፡፡
የዘንድሮው የችግኝ ተከላ በወል መሬቶች፣ በግለሰብ ማሳዎች፣ በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ዙሪያ እየተከናወነ ሲሆን የፍራፍሬ ችግኞችን በአብዛኛው በግለሰብ መሬቶች ላይ መተከላቸውንም ነው የተገለፀው፡፡
እስከአሁን በኦሮሚያ ከ3 ቢሊየን በላይ፣ በደቡብ 8 መቶ ሚሊየን፣ በአማራ 5 መቶ ሚሊየን፣ በሲዳማ 150 ሚሊየን ችግኞችን መተከላቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

