Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ113 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) በቦስተንና አትላንታ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ113 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ፡፡
በወቅቱ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የድርድር ሂደትና ዳያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን÷ ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች እንዲሁም የኤምባሲ አገልግሎትና የኢንቨስትመንት ድጋፍም ተዳሰዋል።
በውይይት መድረኮቹ ማጠቃለያም ከአትላንታ መድረክ ከ33ሺህ ዶላር በላይ እንዲሁም ከቦስተን መድረክ 80ሺህ ዶላር በድምሩ ከ113ሺህ ዶላር በላይ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በልገሳ መልክ መሰብሰቡን ከዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version