አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በሳዑዲ አረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሌንጮ ባቲ የሳዑዲ ግብርና እና እንሰሣት ሃብት ኢንቨስትመንት ኩባንያ ዋና ሃላፊ ሱለይማን አብዱልረህማን ሩማይህ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ በግብርና እና በእንሰሣት ሃብት ልማት ዙሪያ በሚጠናከርበት ሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።
በተጨማሪም ሃገራቱ በምግብ ደህንነት የትብብር መስክ በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ዙሪያ መግባባት መቻሉን በሳዑዲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

