Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 47ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ጉባዔው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን መጨረሻው ይሆናል።
ምክር ቤቱ በቆይታው የአስፈጻሚውና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2013 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ የዳኞች ሹመት፣ የአስተዳደሩን የ2014 በጀትና መሪ እቅድ ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የመሬት ምዝገባ ጽህፈት ቤት ረቂቅ ዓዋጅ ላይ እንደሚወያይ ኢዜአ ዘግቧል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version