አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ህግ በማስከበር ዘመቻ ለሚሳተፉ የመከላከያ ሰራዊትና ለጸጥታ አካላት ደም ለግሰዋል፡፡
የደም ልገሳውን ያካሄዱት ከ210 በላይ የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በመርሃግብሩ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙ የሃገር መከላከያ ሰራዊትና የጸጥታ አካላት ደማችንን በመለገስ ወገናዊነታችንን የምናሳይበት በጎ ተግባር በመሆኑ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ደም መለገሳቸውን ገልፀዋል፡፡
እንዲሁም ሀገራችን ከተጋረጠባት ፈተና ለመታደግ አንድነታችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ ልናጠናክር ይገባል ማለታቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በደም ልገሳው የተሳተፉት የተቋሙ ሰራተኞች በበኩላቸው ÷ሃገር ለማዳን የህይወት መስዋእትነት እየከፈለ ላለው መከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ ከሰራዊታችን ጎን መሆናችንን የምናሳይበት ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

