Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከኢትዮጵያ የታይላንድ አምባሳደር ጋር ተወየዩ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከኢትዮጵያ የታይላንድ አምባሳደር ሳስሪት ታንጉልራት ጋር ተወየዩ ፡፡
በውይይታቸው ኮሚሽነር ለሊሴ የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አምራጮችን ለአምባሳደሯ ገለፃ አድርገዋል፡፡
እንዲሁም የታይላንድ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡና ኢንቨስት እንዲያደርጉ የማስተዋወቅ ስራ መስራትና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም ኮሚሽነሯ ለአምባሳደር ሳስሪት አዲሱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን እድሳትና ገፅታ ማስጎብኘታቸውን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version