Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የወላይታ እና የሃድያ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

የወላይታ ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 9 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የዞኑ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ፀጋ ፋንታ÷ ሀገራችን ድልን እስክትቀዳጅ ድረስ ድጋፋችንን እንቀጥላለን ሲሆን 196 ዩኒት ደም ልገሳ መደረጉንም ገልፀዋል።
የተደረገው የገንዘብና የአይነት ድጋፍ እንደ ዞን ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑንም ተጠቁሟል።
በተመሳሳይ በሀዲያ ዞን ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት በአይነትና በገንዘብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉ በዞኑ ከሚገኙ የወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች፣ ከተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሁም ሰራተኞች የተሰበሰበ መሆኑን የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ደገፈ ኤርጡሞ አስታውቀዋል።
ድጋፉ በቀጣይ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን መግለጻቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version