አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከ 3 ሺህ በላይ ተማሪዎች በነገው እለት ያስመርቃል፡፡
ዩኒቨርስቲው በመደበኛ፣ በተከታታይ፣ በርቀትና በክረምት መርሃግብሮች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 388 ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው።
ተመራቂ ተማሪዎች በተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ፣ በህግ፣ በግብርና፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽንና በሌሎች የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆኑን ከዩኒቨርስቲው የውጭ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በሙክታር ጠሃ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

