Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዲላ ዩኒቨርሲቲ 3ሺህ 468 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 3ሺህ 468 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል፡፡

ለ23ኛ ጊዜ እያስመረቀ የሚገኘው የዲላ ዩኒቨርሲ ስራውን በ400 ተማሪዎች የጀመረ ሲሆን÷ አሁን ላይ 26ሺህ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ከ71ሺህ በላይ ተማሪዎች ሲያስመርቅ÷ ዘንድሮም በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ 3ሺህ 468 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በአራት ካምፓሶቹ ውስጥ ሁለት ኢንስቲትዩት ሰባት ኮሌጆች አሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version