አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)10 ሺህ ህፃናትን ተጠቃሚ የሚያደርግ “መልካም እጆች ለኢትዮጵያ ልጆች”የበጎነት ጉዞ በይፋ ተጀመረ።
መርሃ ግብሩ በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡና መማር ያልቻሉ ህፃናት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጿል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሁሪያ አሊ፣የሴቶች ወጣቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ቡሎ እንዲሁም የክልልና የከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች ፣ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ተገኝተዋል።
ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ “ወሰን ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት ተግባራት
የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር ረገድ ሚናቸው ከፍተኛ ነው።”ብለዋል።
“መልካም እጆች ለኢትዮጵያ ልጆች” የተሰኘው መርሃ-ግብር የተዘጋጀው በወጣት ኢትዮጵያዊያን በተመሠረተው”ብርቱ ተስፋ የህፃናት መርጃ ማዕከል”ሲሆን ከለጋስ ኢትዮጵያዊያን የተሰበሰቡ የመማሪያ ቁሳቁሶች በስምንት ከተሞች ለሚገኙ ህፃናት የሚደርሳቸው ይሆናል።
በዚህም ሐመር፣ቻግኒ፣ድሬዳዋ፣ወላይታ ሶዶ፣መተሀራ፣አርባምንጭ ፣ሆሳዕና እና ቱሉ ቦሎ ከተሞች የመርሃ ግብሩ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ በእነዚህ ከተሞች የሚገኙና በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ልጆችም ተጠቃሚ ይሆናሉ።
በሞሊቶ ኤልያስ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

