Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጅማ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ እየሰራ ያለው ስራ እንደአርዓያ ሊወሰድ እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ እየሰራ ያለውን ስራ ሌሎች በአርአያነት ሊወስዱት እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ ከጂማ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መስክ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
የዩኒቨርሲቲው ዶክተር ፕሬዝዳንት ጀማል አባፊጣ ዩኒቨርሲቲው የህክምና መሳሪያዎችን በራሱ አቅም በመንደፍና በማምረት ወደ ገበያ የገቡ መኖራቸውን ተናግረዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂው ዘርፍ የፈጠረው አቅም ለሌሎች መማሪያ እንዲሆን በቅርብ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎችን በዩኒቨርሲቲው ክላስተር ስር ማደረጀት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ከውጭ የሚመጡ እቃዎችን በሀገር ውስጥ መተካት የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ ይረዳል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የተማሪዎችን የፈጠራ ስራዎች ወደ ገበያ ለማስገባት የሚደረገውን ጥረት ሚኒስቴሩ እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል።
አመራሮቹ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብርም ማከናወናቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version