Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ተግባር የሚያወግዝ ሰልፍ በባስኬቶ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) -የአለም አቀፍ የጦር ህግ ስምምነትን በመጣስ ህፃናትን በጦርነት የማገደውን አሸባሪውን የህወሓት ቡድን አስፀያፊ ተግባር የሚያወግዝ ሰልፍ በባስኬቶ ልዩ ወረዳ ተካሄደ።
በመርሐ ግብሩ ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ለመከላከያ ሠራዊት ተበርክቷል፡፡
የልዩ ወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ታመነ ታምርሶ የአለም አቀፉን የጦር ስምምነት ህግ ወደ ጎን በመተው ህፃናትን ለጦርነት የማገደው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ግብዓተ መሬት ለማፋጠን ሁሉም የወረዳው ህዝቦች ከመከላከያ ጎን በመሰለፍ የኢትዮጵያን ህልውና ማስጠበቅ እንደሚገባ መናገራቸውን የዘገበው ደሬቴድ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version