Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጥቁር ገበያ ሊሸጥ የነበረ ሽጉጥና የተለያዩ ጥይቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ፖሊስና በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ቅንጅት በጥቁር ገበያ ሊሸጥ የነበረ ሽጉጥና የተለያዩ ጥይቶችን ከእነ ተጠርጣሪዎቹ እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡
እንዲሁም ከእህል ጋር ተደባልቆ ወደ ክልል ሊጓጓዝ የነበረ ጥይት በህብረተሰቡ ትብብር መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ሁለቱ አካላት ከህብረተሰቡ በደረሳቸው መረጃ መሰረት ባደረጉት ክትትል ሦስት ግለሰቦች በቢጫ ታክሲ 25 ቱርክ ሰራሽ ኢኮልፒ ሽጉጥ ፣ 586 ፍሬ የኢኮልፒ ሽጉጥ ጥይት ፣ 69 ፍሬ የብሬን ጥይት በጥቁር ገበያ በመገበያየት ላይ እንዳሉ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ዘነበወርቅ አካባቢ ሀምሌ 28 ቀን 2013 ዓም እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ ሀምሌ 23 ቀን 2013 ዓም አንድ ግለሰብ 730 ፍሬ የክላሽን ኮቭ ጥይት ከገብስ ጋር በመቀላቀል ወደ ስልጤ ዞን ለማዘዋወር ሲሞክር በዘነበ ወርቅ መናኸሪያ ተይዟል፡፡
በጥቁር ገበያ የጦር መሳሪያ ሲገበያዩ የተገኙት ሦስት ተጠርጣሪዎችና የክላሽን ኮቭ ጥይት ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ ታስረው ጉዳያቸው እየተጠራ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ በተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የአውቶቡስ መናኸሪያ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች እያበረከቱት ያለው አስተዋፅኦ አበረታች መሆኑን ያነሳው ኮሚሽኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version