አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የአንድ ወር ደሞዛቸዉን ለገሱ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄደዋል፡፡
የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶክተር ምስራቅ መኮንን እንዳሉት÷ በተባበረ ክንዳችን የውስጥና የውጪ ፀረ ሠላም ኃይሎችን ልንመክት ይገባል ብለዋል፡፡
አያይዘውም ሠራተኞች በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ ምንጫቸው ያልታወቁ መረጃ ዎችን ከመጠቀምና በመረጃ ከመረበሽ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡
አስተያየተቸውን የሰጡን ሠራተኞች ሃገሪቱ ካለፉት 3 ዓመታት ወዲህ በርካታ ተግዳሮቶች እንደገጠሟት አስታውሰው÷ ይህ ተግዳሮት እየተባባሰ መጥቶ ሃገርን ለማፍረስ እስከመፈለግ መድረሱን ገልፀዋል፡፡
‘’ሃገር ሰላም ስትሆን ነዉ ዜጎች በሰላም ወጥተዉ የሚገቡት’’ ያሉት አስተያት ሰጪዎቹ÷ የዜጎችን ደህንነትና የሀገርን ሉአላዊነት ለማስከበር ከደመወዛቸዉ በተጨማሪ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ የመጣዉን ጠላት ለመመከት እንደሚዘምቱ አረጋግጠዋል፡፡
ከዚያም ባለፈ የምክር ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞችን ነገ ነሃሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም የደም ልገሳ መርሓ ግብር እንደሚያከናዉኑም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

