Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኦሮሚያ ክልል ሴቶች ፣ ህፃናትና ወጣቶች ለመከላከያ ሰራዊት 12 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት  ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች  ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት የ 12 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ  አደረጉ፡፡

ድጋፉን የኦሮሚያ ክልል ሴቶች ፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሳዓዳ ኡስማን፥ ለመከላከያ የፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ለወዘይሮ ማርታ ሉዊጂ አስረክበዋል።

ወይዘሮ ሳዓዳ ክልሉ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ጁንታውንና ተላላኪዎችን በመደምሰስ የሀገር ህልውናን ከአደጋ ለመታደግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል ።

ወይዘሮ ማርታ በበኩላቸው፥ ሴቶች ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በህግ ማስከበሩ ወቅት ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው አስታውሰው ለተደረገው ድጋፍ ማመስገናቸውን ከመከላካያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version