አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የ34ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች የመክፈቻ ስነ‐ስርዓት አካሄደ።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዘዥ ኮሎኔል ጌታቸው አሊ÷ ሀገራችሁን በቅንነት ለማገልገል የውትድርና ሙያ በመምረጥ በሀገራችን የሚቃጣውን ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከል ፣ አሸባሪውን የጁንታ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ፣ህዝብና ሃገርን ለመጠበቅ ጀግንነት የተሞላበት ውሳኔ ወስናችሁ እንኳን የጀግኖች መፍለቂያ ወደ ሆነው ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በሰላም መጣችሁ ብለዋል።
ከምልምል ሰልጣኞች መካክል አመሃ አሻግሬ እና ትግስት ሽበሽ ÷በሰጡት አስተያየት፣ ውትድርና ሞያን ከልጅነታቸው ጀምሮ እንደሚወዱትና ወታደር ለመሆን በመብቃቸው መደሰታቸውን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላከትል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

