አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ለኮቪድ 19 የሚደረገው ጥንቃቄ መዘናጋት እንዳሳሰበው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ ከፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት ከትናንት ምሽት ዜና መጽሄት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት÷ የህብረተሰቡ መዘናጋትና ቸልተኝነት ያሳስባል ።
መንግስት ዜጎች እንዲጠነቀቁ ለማድረግ የተለያዩ ንቅናቄዎችን እያደረገ ቢሆንም ማህበረተሰቡ ተዘናግቷል ብለዋል ።
በኢትዮጵያ የቫይረሱ ስርጭት ከዚህ በፊት ከነበረው አሁን ቁጥር ጨምሯል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው÷ የጽኑ ህሙማን ክፍሎችም እየተጨናነቁ ናቸው ብለዋል ።
የኮቪድ 19 ምርምራ አሁን ላይ በርካታ ሰዎች በሚገኙበት ቦታ እና በኬላዎች አካባቢ ላይ ተጠናከሮ መቀጠሉንም ተናግረዋል ።
በቀጣይ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች ትኩረት እንዲያደረጉ የተለየ ዝግጅት ላይ እንገኛለንም ብለዋል ።
የመተንፈሸ መሳሪያዎች እጥረት እና ህክምና መስጫ ተቋማት እየሞሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል ።
በሃይለየሱስ መኮንን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

