አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 2 ሺህ 243 የእርድ እንስሳትና የስንቅ ድጋፍ አድርገዋል።
የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች 609 ሰንጋ፣ 1 ሺህ 634 በጎች እና 900 ሺህ 618 ብር ግምት ያለው የስንቅ ድጋፍ አድርገዋል።
የተደረገው ድጋፍ አጠቃላይ በገንዘብ ሲተመን ከ85 ሚሊዮን 700 ሺህ ብር በላይ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አሸባሪው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የጀመረውን አንቅሳቃሴ ለመመከት ኢትዮጵያዊያን በገንዘብም በጉልበትም ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

