አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ዕዝ ለሽብር ቡድኑ ሊደርስ የነበረ ከ5 ሺህ በላይ የክላሽ ጥይት መያዙን አስታወቀ፡፡
የምዕራብ ዕዝ ዘመቻ ሃይል ክትትል ተወካይ ሻለቃ ጌታቸው ዋሬ ÷ ጥይቱ በሁለት ቋጠሮ ተደርጎ በአህያ ተጭኖ ለሽብር ቡድኑ ሊደርስ ሲል ጫካ ውስጥ እንደተያዘ ተናግረዋል፡፡
ጥይቱ ወደ ቡድኑ ቢደርስ የሚያስከትለው ጉዳት የከፋ ይሆን እንደነበር ነው ሻለቃ ጌታቸው የገለጹት፡፡
የሽብር ቡድኑ የሚያገኛቸውን ሎጀስቲካዊ ሆነ ሌሎች ድጋፎች ተከታትሎ በአልታሰበ ጊዜ በቁጥጥር ስር ማድረግ ቡድኑን የበለጠ ያዳክመዋል ያሉት፡፡
ሰራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ ያልተቋረጠ ስራ እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ጥይቱን በቁጥጥር ስር ካዋሉት የምዕራብ ዕዝ ደጀን ጥበቃ አባላት መካከል ሃምሳ አለቃ አብዲ ዓሜ እና ሃምሳ አለቃ ዮሀንስ ባይከዳ ÷ጥይቱ በተላላኪዎች በኩል ሊደርስ እንደነበርና በትኩረትና በጥንቃቄ በማሰስና በመፈተሽ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

